የእለት ዜና

“መንግስትና ህብረተሰቡ የሚያደርግልን ድጋፍ በፍትሃዊነት ሊደርሰን ይገባል”፡- በደሴ ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች

በመንግስትና በህብረተሰቡ የሚደረግላቸው ድጋፍ በፍትሃዊነት እየደረሳቸው ባለመሆኑ እንዲስተካከል በደሴ ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ጠየቁ።

የጅማ ዩኒቨርሲቲና ዶክተር አረጋ ይርዳው በህወሓት ቡድን ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች የእለት ደራሽ ምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ በዛሬው እለት አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅት ከተፈናቃዮች መካከል የሱፍ አደም እንዳሉት፤ በህወሃት ቡድን ምክንያት ከሐራ ከተማ ተፈናቅለው የእለት ደራሽ ምግብ እንዲጠብቁ ተገደዋል።

”ችግራችንን የተረዱ ግለሰቦች፣ ተቋማትና መንግስት የእለት ደራሽ ምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ እያደረጉልን ቢሆንም እርዳታው በፍትሃዊ መንገድ እየደረሰን አይደለም” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሚመለከተው አካል ችግሩን በአስቸኳይ እንዲፈታ የጠየቁት የሱፍ ቅድሚያ ማግኘት የሚጠበቅባቸው ሴቶችና አዛውንቶች እያሉ ጉልበተኞች ከቤተሰቦቻቸው ቁጥር በላይ በተደጋጋሚ በመውሰድ ጭምር የእርዳታው ፍትሃዊነት እንዲዛባ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com