የእለት ዜና

ወርቁ አይተነው በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊትና ለተፈናቀሉ ዜጎች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

ባለሃብቱ ወርቁ አይተነው በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊትና አጠቃላይ የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች፣ እንዲሁም ለሰሜን ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች የሚውል የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ባለሃብቱ ድጋፉን በደባርቅ ከተማ ተገኝተው ለሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ደብረወርቅ ይግዛው አስረክበዋል።

ወርቁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድንን በአጭር ጊዜ ለማስወገድ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት እና በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

በቡድኑ ወረራ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ተቋማት እና ባለሃብቶች የበኩላቸውንእንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለሃብቱ በቀጣይ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም የተናገሩ ሲሆን፤ የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ግባታቸውም የሚታወስ ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com