የእለት ዜና

ምክር ቤቱ አራት የዲጂታል መተግበሪያዎችን ይፋ አደረገ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሰራርን የሚያሻሽሉ አራት ዲጂታል መተግበሪያዎች ይፋ ተደርገዋል።

መተግበሪያዎቹ መረጃን በቀላሉ ለመለዋወጥ የሚያስችሉ እና የተደራሽነት ችግርን የሚቀርፉ ናቸው ተብሏል።

በመተግበሪያዎቹ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ መተግበሪያዎቹ ከ1934 ጀምሮ በምክር ቤቱ የሚገኙ ቃለ ጉባኤዎች እና ሰነዶችን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላሉ ብለዋል።

መረጃን ለማግኘት ይወስድ የነበረውን ጊዜ እና ገንዘብን የሚቆጥቡ፣ ህዝብ እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን ግንኙነትም የሚያጠናክሩ መሆናቸውንም አፈ ጉባኤው ገልጸዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!