የእለት ዜና

ለ2014 በጀት ዓመት የአማራ ክልል ምክር ቤት 80.1 ቢሊዮን ብር አፀደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የመጨረሻ ጉባዔው ለ2014 በጀት ዓመት 80.1 ቢሊዮን ብር በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በጀቱ ወቅታዊ የክልሉን እና የሀገሪቱን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

ተሰናባች የምክር ቤት አባላት የህወሓት የሽብር ቡድን በክልሉ አምስት ዞኖች የፈፀመው ወረራ ያደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት ተጨማሪ በጀት እንዲኖር ጠይቀዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የህወሓት ቡድን ጉዳት ያደረሰባቸው አካባቢዎችን ለመልሶ ግንባታ የሚውል ሀብት የማሰበሰብ ሥራ በስፋት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ ድጋፍ እና በጀት እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርበናል ብለዋል።

አገኘሁ የአማራ ክልል ሕዝብ፣ የተለያዩ ክልሎች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኅልውና ዘመቻ እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤ ዳያስፖራው ለኅልውና ዘመቻው አይነተኛ ድጋፍ እያደረገ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በተጨማሪም የህወሓት ቡድን በርካታ የጤና ተቋማትን ማውደሙን ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ገልጸው፤ ቡድኑን ለመደምሰስ እየተሠራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com