የእለት ዜና

የሰላም ሚኒስትሯ ከአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭትና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ተወያዩ

የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭት ሂደት ላይ ከአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ስርጭትና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ተወያይተዋል።

በአማራ እና አፋር ክልል ላይ እየተካሄደ ባለው የእርዳታ ስርጭት ላይ የታዩ ክፍተቶችን እና ሊወሰዱ የሚገቡ አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ ዝርዝር ውይይት ማካሄዳቸውም ተገልጿል።

በውይታቸውም ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ለማድረስ የየዕለት ግብ የተያዘ ቢሆንም ወደ ክልሉ ገብተው ባልተመለሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች ምክንያት ሂደቱ መስተጓጎሉ ተነስቷል።

ተሽከርካሪዎቹን በማስመለስ ረገድ የሰብዓዊ እርዳታ ሰጭና አቅራቢ ድርጅቶቹ ሃላፊነት ወስደው ተገቢውን አመራር በመስጠት መመለሳቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!