የእለት ዜና

ነገ ምርጫ በሚካሄድባቸው አከባቢዎች ሥራ ዝግ ይሆናል:- ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ነገ መስከረም 20/2014 የ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ኹለተኛው ዙር በሚካሄድባቸው አከባቢዎች ሥራ ዝግ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ነገ ምርጫ የሚካሄድባቸዉ ሶማሌ እና ሐረሪ ክልል ሙሉ በሙሉ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በ11 ዞኖች እና በአንድ ልዩ ወረዳ ይካሄዳል።

ለምርጫዉ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ሐረሪ ክልል ሙሉ በሙሉ የተሰራጩ ሲሆን፣ በሶማሌ ክልል በአምስት ምርጫ ክልሎች እሰካሁን ድረስ አልደረሱም ተብሏል።

ይሁን እንጂ ማምሻዉን ተሰራጭተዉ እንደሚጠናቀቁ ቦርዱ ገልጿል።

______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!