የእለት ዜና

ከዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አንዳንድ መንገዶች ለጊዜዉ ዝግ ይሆናሉ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ የሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን ከዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አንዳንድ መንገዶች ለጊዜዉ ዝግ እንደሚሆኑም ገልጿል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከሀገር መከላከያ ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከፌዴራል ፣ ከኦሮሚያና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ከአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ ልዩ ልዩ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱንም ገልጿል፡፡

የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ለወንጀል መከላከል ተግባራቸው ልዩ ትኩረት በመስጠት አብዛኛውን የሰው ኃይላቸውን በወንጀል መከላል ስራ ላይ ማሰማራታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅሶ፤ በተለይ በዓሉ ወደ እሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዘበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ወሳኝ ስራ ማከናወኑን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ የዘንድሮው የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል በሰላም እንዲከበር የበዓሉ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ በፀጥታ አካለት ስም ጥሪውን አስተላፏል፡፡

የኢሬቻ ሆራ ፊንፍኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜዉ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችንም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ

=} ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚውስደው መንገድ 22 ማዞሪያ

=} ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ በፓርላማ መብራት
=} በቸርችር ጎዳና ፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

=} ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

=} ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሳር ቤት አደባባይ

=} ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ

=} ከቦሌ ፣ በአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ከርስቲያን የሚወስደው መንገድ ኤድናሞል አደባባይ

=} ከአዋሬ ወደ ካሳንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

=} ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ አካባቢ ለጊዜው ዝግ እንደሚሆኑ ገልጿል።
በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም እንሚቻልም አስታውቋል።
__________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!