የእለት ዜና

10 በዓለም ላይ ከፍተኛ ሽያጭ ያላቸው ዝነኛ ተንቀሳቃሽ ስልኮች

ምንጭ፡-፡- ማኑፋክቸሪንግ ግሎባል (2021)

በዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስልኮች አሠራራቸው እየተሻሻለና እየዘመነ መምጣቱ ይታወቃል። ከስልኮቹ መለያ ወይም ብራንድ ዝና ጋር ተያይዞም በዓለም ላይ ያሉ ተጠቃሚዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ እንደመጣ መረጃዎች ያመላክታሉ። ከላይ በዐስርቱ የተዘረዘሩት የተንቀሳቃሽ ስልክ ዓይነቶችም በአንድ ዓመት ውስጥ በዓለም አገራት ብዛት ያለውን ስርጭት በመያዝ እንደተሸጡ ተመላክቷል።
‹ማኑፋክቸሪንግ ግሎባል› የተሰኘ ድረገጽ ባለንበት የፈረንጆች ዓመት 2021 ባወጣው ዘገባ መሠረት፣ 83 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ እንደሚጠቀም ተረጋግጧል። ይህን ተከትሎም በዓመት ውስጥ የስልክ ቀፎ ግብይቱ እንደጨመረ ነው ዘገባው የጠቆመው።
ከላይ ከተዘረዘሩት ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎች መካከል ሳምሰንግ በዓመት ውስጥ 315 ሚሊዮን ምርቶችን ለደንበኞቹ የሸጠ ሲሆን፣ በዚህም የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ የዓለምን ገበያ ተቆጣጥሯል። ከዛም በመቀጠል አፕል ምርቶቹ የሆኑ የስልኮችን በዓመት እስከ 251 ሚሊዮን በመሸጥ ኹለተኛውን ደረጃ ሲይዝ፤ አልካቴል ሉሰንት ዐስረኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።


ቅጽ 3 ቁጥር 152 መስከረም 22 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com