የእለት ዜና

ለስድስት ኩባንያዎች የከፍተኛ ማዕድን ምርት ፈቃድ ተሰጠ

ለስድስት ኩባንያዎች የከፍተኛ ማዕድን ምርት ፈቃድ መሰጠቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ገለጸ።
ኩባንያዎቹ ፈቃድ የተሰጣቸው የማዕድን ፍለጋውን አጠናቀውና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማሟላት መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ኩርሙክ ጎልድ ማይን፣ ኢትኖ ማይኒንግ እና ኦሮሚያ ማይኒንግ ኩባንያዎች የወርቅ ምርት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
እንዲሁም አሊ ሀሚል ካሐዲም የብሮሚን እና ክሎሪን ምርት ፈቃድ ሲወስድ፣ ኪሪፕቶ ማይኒንግ ኤንድ ኬሚካልስ እና ቡሁሚ ማይኒንግ ኩባንያዎች ደግሞ የእምነ በረድ ምርት ፈቃድ መውሰዳቸው ነው የተመላከተው።
ስምምነቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የኩባንያዎቹ ሥራ አስኪያጆች ተፈራርመዋል።
ኩባንያዎቹ ከ4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፤ ከ 1 ሺሕ 300 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩንም የማዕድና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታውቋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 152 መስከረም 22 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!