የእለት ዜና

ከአበባ እርሻ የሚገኝ ተረፈ ምርት ለማዳበሪያ ከሚወጣ ገንዘብ 33 በመቶ መቀነስ ማስቻሉ ተገለጸ

ከአበባ እርሻ የሚገኝ ተረፈ ምርት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ሰው ሠራሽ ለሆነ ማዳበሪያ ከሚያወጡት ገንዘብ እስከ 33 በመቶ የሚሆነውን እያስቀረላቸው መሆኑ ተገለጸ።
አበባዎች ከሚያስገኙት ገቢ በተጨማሪ ተረፈ ምርታቸው እንዲበሰብስ ከተደረገ በኋላ ተመልሶ በፈሳሽ ማዳበሪያ መልክ በብዙ የእርሻ ቦታዎች ላይ እንደማዳበሪያነት እያገለገለ መሆኑ ነው የተመላከተው። በዚህም በአበባ ልማት የተሰማሩ ባለሀብቶች ለእርሻቸው ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ከሚገዙበት ወጪያቸው እስከ 33 በመቶ ቆጥቦላቸዋል ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ በምርት ሂደት ወቅት በሰው ሠራሽ ማዳበሪያ እና መሰል ምክንያቶች የተበከለን ውሃ አክሞ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልም በብዙ የአበባ እርሻዎች እየተሠራ መሆኑ ነው የተመላከተው። እስከ አሁንም በ31 የአበባ እርሻዎች ላይ የተበከለ ውሃን በማጣራት ለዳግም ጥቅም ማዋል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተገንብቶ እየተሠራበት እንደሆነም ተጠቅሷል።
በዐስር የአበባ እርሻዎች ላይ ቴክኖሎጂው እየተገነባ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና ላኪዎች ማኅበር የቆሻሻ አወጋገድ መምሪያ ኃላፊ ቶማስ ተክለሥላሴ ገልጸዋል። በዚህም በቴክኖሎጂው የታከመው ውሃ ለአበቦች እርሻ ጥቅም ላይ ከመዋል ባሻገር አርሶ አደሮችም ለመስኖ ሥራ እየተጠቀሙበት መሆኑ ነው የተመላከተው።


ቅጽ 3 ቁጥር 152 መስከረም 22 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com