የእለት ዜና

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከትላንት በስትያ ጀምሮ የደረሰበት አልታወቀም

የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መስራች እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከትላንት በስትያ ጀምሮ የት እንዳለ አይታወቅም ሲሉ ጓደኞቹ እና የስራ ባልደረቦቹ አስታወቁ።

የጋዜጠኛው ጓደኞች እና የስራ ባልደረቦቹ እንደተናገሩት ከሆነ፤ መስከረም 22/2014 በአዲስ አበባ የተከበረውን የሆራ ፊንፌኔ የኢሬቻ በዓል ከዘገበ በኃላ ተስፋለምን ሊያገኙት እንዳልቻሉና እስከአሁንም ያለበት አለመታወቁን አሳውቀዋል።

ጋዜጠኛው በትናንትናው ዕለት በቢሾፍቱ የተከበረውን የሆራ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓል ለመዘገብ እቅድ እንደነበረውም መግለፆቸውን አዲስ ዘይቤ ዘግቧል።
__________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!