የእለት ዜና

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመትና የአዲስ የመንግስት ምስረታ በዓል እየተከናወነ ነው

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመትና የአዲስ የመንግስት ምስረታ በዓል በመስቀል አደባባይ በመከናወን ላይ ይገኛል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የፌደራል ጦር ሃይሎች፣ የአየር ሃይል፣ የምድር ሃይል እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ የልዩ ዘመቻ ኮማንዶዎች ወታደራዊ ትርዒት አቅርበዋል።

በበዓለ ሲመቱ ላይ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

በተጨማሪም የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮችም በዓለ ሲመቱን በመታደም ላይ ይገኛሉ።

በአሁኑ ወቅትም ከተለያዩ አገራት በዓለ ሲመቱንና የአዲስ የመንግስት ምስረታውን ለመታደም የተገኙ መሪዎች ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!