የእለት ዜና

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ርዕይና ሥራዎች የሚያስቀጥል ፋውንዴሽን ተመሠረተ

የተመራማሪ፣ መምህር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ደራሲ፣ የሠላማዊ ትግል አቀንቃኝ እና የፍትሕ ተቆርቋሪ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዕረፍት 1ኛ ዓመት መታሰቢያና በስማቸው በተቋቋመው ፋውንዴሽን ምሥረታ ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም የፊታችን መስከረም 29 ቀን 2014 በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የፋውንዴሽኑ ሊቀመንበር ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ እንዳሉት፣ ፕሮፌሰር መስፍን ሙሉ ሕይወታቸውን ለአገር የሰጡ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ከድህነት የተላቀቀች፣ ሠላም፣ ሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ለማድረግ ሲሠሩ ነበርም ተብሏል።
በፕሮፌሰሩ ስም የተመሰረተው ፋውንዴሽን በማኅበረሰብ ሳይንስና በሠብዓዊ መብት ላይ ምርምር ለሚያካሂዱ ዜጎች ድጋፍ ያደርጋል። እንዲሁም ፋውንዴሽኑ ዓመታዊ ዓውደ ጥናት በማዘጋጀት የጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲካሄዱ ያደርጋልም ተብሏል።
በልዩ የመታሰቢያ ፕሮግራሙም፣ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ታላላቅ ምኑራን፣ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ሰዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት አመራሮች፣ ገጣሚያን፣ የጥበብ ባለሙያዎች፣ የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ተማሪዎቻቸው፣ እንዲሁም ሌሎችም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ነው የተዘከረው።
በመታሰቢያ ፕሮግራሙ በተለይ ‹ሠላምና የግጭት አፈታት ተሞክሮዎች በኢትዮጵያ የፕሮፌሰር መስፍን የሰላማዊ ትግል መርሆዎችና ምላሽ ያላገኙ የሠላም ጥሪዎች› የሰብዓዊ መብቶች የሕግ የበላይነት እና የማኅበራዊ ፍትሕ መከበር ጥያቄ በኢትዮጵያ የኢሰመጉ ልደት
ዕድገት፣ ተጋድሎ እና የፕሮፈሰር መስፍን ሚና፣ ኢትዮጵያን ከድህነትና ከችግር ለማላቀቅ የተደረጉ ጥረቶችና ቀጣይ ተግዳሮቶች፣ በሚሉ ጥናታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የሆነ ውይይት ይካሄዳልም ተብሏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 153 መስከረም 29 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com