የእለት ዜና

ከሰሐራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮችን ኢኮኖሚ በ3 ነጥብ 3 በመቶ ለማሳደግ የዓለም ባንክ ፕሮጀክት የነደፈ መሆኑን አስታወቀ

የአፍሪካ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከቻይና ፈጣን ዕድገት ጋር ሲነፃፀር በ2021 የመጀመሪያ አጋማሽ የአፍሪካን የወጪ ንግድ ሊያጠናክር ይችላል ተብሏል።
ዓለም አቀፉ አበዳሪ ድርጅት የዓለም ባንክ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን በ2022 እና በ 2023 ከ 3 በመቶ በላይ ተግባራዊ እንደሚያደርግም ገልጿል።
ከ2020 በኋላ የአፍሪካ ኢኮኖሚ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ እንደተጎዳ ጥናቶች እንዳሳዩ የተገለጸ ሲሆን፣ ውጤታማ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት ሕይወትን ለማዳን እና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ማገገም ቁልፍ ሚና አለው ተብሏል። የአፍሪካ አገራት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክስተት አንስቶ የመዋቅር እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ማጎልበታቸው እንዲሁ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም፣ ከሰሐራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚ የማገገም ሂደት ለማፋጠን የዓለም ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል ነው የተባለው።


ቅጽ 3 ቁጥር 153 መስከረም 29 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com