የእለት ዜና

የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በባቡር መስመር ላይ በሚፈጠሩ ችግሮች ምክንያት ሥራው ተስተጓጉሏል ተብሏል

የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ትራንስፖርት ዘርፍ በማቀላጠፍ የጀርባ አጥንት ነው ተብሎ በሚታመንበት በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ደኅንነት ዙሪያ በአዳማ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ በአንድ ጉዞ ብቻ ከ2 ሺህ 100 ቶን በላይ ዕቃ በማጓጓዝ የኢትዮጵያን የወጪ እና ገቢ ትራንስፖርት ለማቀላጠፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ተብሎ የሚታመንበት የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ አሁን ላይ በሚያጋጥሙት የተለያዩ ችግሮች ምክንያት መስተጓጎል እያጋጠመው ነው ተብሏል። በዚህም ስርቆት፣ የእንስሳት አደጋ እና እገታ ለአገልግሎቱ መስተጓጎል ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው ተብሏል።
የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች እንዳይከሰቱ ሕብረተሰቡ ከሐዲዱ መስመር ሊርቅና ሊጠበቅ፣ እንስሳትንም ሊጠብቅ ይገባል ተብሏል። ባለፉት ዓመታት በባቡር ትራንስፖርቱ ላይ ከፍተኛ የሥርቆት፣ የጸጥታ እና የአደጋ ችግሮች ሲያጋጥሙ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡
በሰፊው ይስተዋል የነበረው ይህ ችግር በብዙ አካባቢዎች መሻሻል ቢታይበትም፣ በባቡሩ መተላለፊያ መስመሮች በሚገኙት በአዳማ፣ በቢሾፍቱ እና ፊጦ ባሉ መስመሮች መካከል ችግሩ አሁንም እንዳለ ነው የተነገረው፡፡
በተለይም በዚህ ድርጊት ላይ የተሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው ሕጋዊ እርምጃም የላላ ነው ተብሏል።
ችግሩን ለማስወገድ የየአካባቢው የጸጥታ አካላትና የሕብረተሰቡ ትብብር ወሳኝ እንደሆነም ተጠቁሟል።


ቅጽ 3 ቁጥር 153 መስከረም 29 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com