የእለት ዜና

የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት ላይ ማሻሻያ ተደረገ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያና ማስተማሪያ መጻሕፍት ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ተገለጸ።
በተደረገው ማሻሻያ ላይ ባለድርሻ አካላት ውይይት ያካሄዱ ሲሆን፣ መጻሕፍቱን በሙከራ ደረጃ በዚህ ዓመት በማስተማር ለማስጀመር እንደታሰበም ነው የተመላከተው።
የትምህርት ቢሮው የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር ካሴ አባተ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ከሆነ፣ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ መጻሕፍት ላይ መሠረታዊ ማሻሻያዎች መደረጉን ነው።
የተደረገው የሥርዓተ ትምህርት ማሻሻያ አዲሱን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ አገር በቀል እውቀቶችና እውቀት ተኮር ሐሳቦች እንዲካተቱ፣ እንዲሁም የልዩ ፍላጎትን እና ሥርዓተ ፆታን ያማከሉ እንዲሆኑ ተደርጓል ነው ያሉት ዳይሬክተሩ።
በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ጀነራል ዳይሬክተር የሆኑት ቴዎድሮስ ሸዋረጋ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ከሆነ፣ የሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ሒደት በመሆኑ በየጊዜው የሚታዩ ክፍተቶችን በማስተካከል በእውቀትና ክህሎት የታነጸ ትውልድ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
የተሻሻሉት መጻሕፍት በዘንድሮ በሙከራ ደረጃ የሚቀርቡ መሆናቸውን የገለጹት ቴዎድሮስ (ዶ/ር) በሒደት የሚጠናቀቀውን የማሻሻያ ሥራ ውጤታማ ለማድረግም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ሲሉ ገልጸዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 153 መስከረም 29 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com