የእለት ዜና

ተቋማት በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

ተቋማት በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳስቧል፡፡

ኤጀንሲው የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ጠላቶች እና ተባባሪዎቻቸው ከውስጥና ከውጭ ሆነው የሳይበር ምህዳሩን በመጠቀም በተለያዩ የመሰረተ-ልማትና የመረጃ አውታሮች ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ለመፈጸም ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ገልጿል፡፡

ነገር ግን ሀገራችን አሁን እያከናወነችዉ ካለችው የህግ ማስከበርና የህልዉና ዘመቻ ጋር እንዲሁም ሌሎች ቀጠናዊና አለምአቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ አሁን እየታዩ ያሉት አዝማሚያዎችና ሙከራዎቻቸውን ማሳሰብና ማሳውቅ አስፈልጓል ብሏል፡፡

እነዚህ እኩይ ዓላማ ያላቸው አካላት እዚሁ ሀገር ዉስጥ ሆነው የመሰረተ-ልማትና የመረጃ አውታሮችን እንዲሁም ሲስተሞችን እንዲያስተዳደሩ በተቋማት መብት የተሰጣቸውን (ሲስተም አድሚኒስ) ለሙያቸው፤ ለተቋማቸውና ለሀገራቸው ታማኝ ያልሆኑ ጥቂት ጡት ነካሽ ባንዳዎችን በመጠቀም እክል ለመፍጠር እየሰሩ ይገኛል ሲልም ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

ስለሆነም ማንኛዉንም የመሰረተ-ልማትና የመረጃ አውታሮችን እንዲሁም ሲስተሞችን የምታስተዳደሩ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት ሲስተሞችን እንዲያስተዳደሩ መብት የተሰጣቸው ወይም የተቋማትን የሶሻል ሚዲያ አካውንቶችን እንዲያስተዳድሩ የይለፍ-ቃል ወይም (ፓስወርድ) እንዲይዙ የተፈቀደላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ወይም (ሲስተም ወይም ኔትወርክ አድሚንስ) ትክክለኛውን የሙያ ብቃት እና ጥብቅ የሥነ-ምግባር ማጣራት የተደረገባቸው መሆኑን ደግማችሁ፣ ደጋግማችሁ እንድታረጋግጡ ሲል ማሳሰቡን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com