የእለት ዜና

አዲስ ለተሾሙ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና እየተሰጠ ነው

በአዲሱ መንግስት ለተሾሙ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በዚህ ስልጠና መክፈቻ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ገለጻ ፤ አመራሩ በንፁህ እጅና በቅንነት አገሩን ማገልገል አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚረጋገጠው ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች በአግባቡ በማልማት፣ በትጋት በመስራትና በንፁህ እጅና በቅንነት መሆኑን መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

አመራሮች ከሥልጠናው በኋላም የዓላማ ጽናት በቡድን የመሥራት መንፈስና በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com