የእለት ዜና

14ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ ነው

14ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉአላዊነት ለሰንደቅ አላማ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።

በተሻሻለው የሰንደቅ ዓላማ ዐዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሰኞ በመላ አገሪቱ እንዲከበር መደንገጉ ይታወቃል።

በዚህ መሠረት “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉአላዊነት ለሰንደቅ አላማ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ግቢ በመከበር ላይ ነው።

በክብረ በዓሉ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዓሉ በተመሳሳይ ሰዓት በመላ የአገሪቱ ክፍሎች እና በተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች በመከበር ላይም ይገኛል።
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com