የእለት ዜና

ከ44 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ባሳለፍነው ሳምንት ከ21/01/2014 እስከ 27/01/2014 ድረስ ከ44 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከአገር ሊወጡ እና ወደ አገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን የገቢ ኮንትሮባንድ 43 ሚሊዮን 12ሺ 009 ብር፤ ወጪ ደግሞ 1ሚሊዮን 437ሺ 851ብር፣ በድምሩ የ44 ሚሊዮን 449ሺ 860ብር ግምት አላቸው ተብሏል፡፡

አቃቂ ቃሊቲ እና ሞያሌ የጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሊያዙ ችለዋል፡፡

ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ ተሽከርካሪ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ አደንዛዥ እጽ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com