የእለት ዜና

ፑራቶስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በ120 ሚሊዮን ብር የፈጠራ ማዕከል መገንባቱን አስታወቀ

ፑራቶስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የዳቦ፣ የኬክና የቸኮሌት ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካና ልዩ የምግብ ፈጠራ ማዕከል ግንበቶያስመረቀ ሲሆን፣ ለፈጠራ ማዕከሉ ግብታ 120 ሚሊዮን ብር እንዲሁም አጠቃላይ ፋባሪካውን እና ማዕከሉን ለማስገንባት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ፑራቶስ ኢትዮጵያ መሰረቱን ቤልጂየም ያደረገው የፑራቶስ ድርጅት አካል ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በዘርፉ ከተሰማራ ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ እንዳስቆጠረ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶሚሊክ ኤድዋርድ ገልጸዋል፡፡ በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ፋብሪካ ከማቋቋም እስከ ፈጠራ ማዕከል መክፈት የደረሱ ሥራዎችን መሥራቱ ተገልጿል፡፡ ድርጅቱ በአዲስ አበባ የገነባው ፋብሪካ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተገጠመለት የፈጠራ ማዕከል እያደገ የመጣውን የደንበኞች ጥራት ፈላጎት ለማሟላት እንደሚያግዝ ተነግሮለታል፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው የፈጠራ ማጭከሉ፣ የድርጅቱን ደንበኞች የፈጠራ ችሎታዎችን የሚዳብሩበት እና ሀሳባቸውን ወደ ተጨባጭ የተዘጋጀ ጣፋጭ ምግቦች የሚለውጡበት የፈጠራ ሥራ ነው ተብሏል፡፡
ፑራቶስ ኢትዮጵያ አገር ውስጥ ያሉ የኬክና ዳቦ ባለሙያዎችን፣ ዓለም ዓቀፍ ሆቴሎችን፣ ሱፐር ማርኬቶችን እና ሬስቶራንቶችን የሚገለግል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በጅቡቲ፣ በሱዳን፣ በሶማሊያ እና በኤርትራ የመሰማራት እቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ ከተሰማራባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬኒያ እና ኮትድባር ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በ1919 ቤልጂየም ብራሰልስ ውስጥ የተቋቋመው ፑራቶስ ለዳቦ፣ ለኬክና ለቸኮሌት ኢንዱስትሪ የተሟላ የፈጠራ ምርቶችን፣ ጥሬ እቃዎችንና በዘርፉ አዳዲስ አሰራሮችን የሚስተዋውቅ ድርጅት ነው ተብሏል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 154 ጥቅምት 6 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com