የእለት ዜና

10 ምርጥ ንቁ ወታደራዊ ኃይል ያላቸው የዓለም አገሮች

ምንጭ፡-፡- ስታቲስታ 2021

የስታቲስታ ድረ ገጽ በ2021 ባመላከተው መረጃ መሰረት በዩናይትድ ስቴትስና በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የወታደራዊ ኃይሎች ንቁ ናቸው የሚባሉት የሙሉ ጊዜ ስራቸው የውትድርና ኃይል አካል የሆነ ግለሰቦች ናቸው።
በመረጃው እንደተመላከተው ከሆነ፤ የአንድ አገር ጦር ኃይሎች ጥንካሬ የሚወሰነው በሰራተኞቹ ብዛት ብቻ ሳይሆን በመሳሪያዎቻቸው ብዛትና ጥራትም ጭምር ሲሆን፤ ቻይና በንቃት በሚንቀሳቀሱ ወታደራዊ ሰራተኞች በዓለም ላይ ከፍተኛ የታጠቁ ኃይሎች እንዳሏት ነው።
እንደ ስታቲስታ ጥናት ገለጻም ከላይ የተዘረዘሩት አስር አገራት በዓለማችን ውስጥ ከፍተኛ ንቁ የውትድርና ኃይል ያላቸው አገሮች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም መካከል ቻይና 2.185.000 ንቁ ወታደሮችን በማደራጀት የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛለች።
ከቻይና ቀጥለው ሕንድና ዩናይትድ ስቴት ኹለተኛና ሦስተኛ ደራጃ ላይ እንደሚገኙ ሲመላከት፡ ከአስሩ ምርጥ መካከል ሳውዲ አረቢያ ደግሞ 480.000 ንቁ የወታደራዊ ኃይል በማደራጀት አስረኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።


ቅጽ 3 ቁጥር 154 ጥቅምት 6 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!