የእለት ዜና

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአልባሳት ማምረት ዘርፍ የ30 ዓመታት ልምድ ካለው የግሪክ ኩባንያ ጋር የውል ስምምነት ማካሄዱን አስታውቀ

የውል ስምምነቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና በዲሚትሪየስ ካምፑሪስ (ካምቦቴስ) ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲሚትሪየስ መካከል እንደተደረገ ተገልጿል።
በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ድርጅቱ ያቀረበው የለማ መሬት ጥያቄ በኮርፖሬሽኑ ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ በ15 ወራት ውስጥ የግንባታ ሥራዎችን አጠናቆ ወደ ተግባር ይገባል ተብሏል።
የዲሚትሪየስ ካምፑሪስ (ካምቦቴስ) በበኩሉ፣ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግ ዕድሉን በማግኘቱ ደስተኛ መሆኑና በተቻለ መጠን በፍጥነት ወደ ሥራ ለመግባት የሚቻለውን ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል።
18,600 ስኩዌር ሜትር የለማ መሬት ለመረከብ የውል ስምምነት የፈረመው አምራች ድርጅቱ፣ ለኢንቨስትመንቱ 486,540, 000 ብር ወይም 11 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ፈሰስ እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል።
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራውን የሚጀምረው ካምቦቴስ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ ከ1 ሺሕ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞችን ለመቅጠር ዕቅድ ያለው ሲሆን፣ ይሄው ድርጅት ምርቶቹን በአውሮፓ በሚገኙ 24 ሱቆቹ እና አዳዲስ በሚከፍታቸው ሱቆች ምርቶቹን ለደንበኞቹ እንደሚያከፋፍል ተገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 155 ጥቅምት 13 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com