የእለት ዜና

10 ምርጥ በዓለም ውስጥ ከፍተኛ ደመወዝ የተከፈላቸው ዶክተሮች

በዓለማችን ውስጥ ለተለያዩ የሕመም አይነቶች ህክምና የመስጠት ሙያ ያላቸው ዶክተሮች እንዳሉ ይነገራል። ከእነዚህም መካከል ከአዕምሮ ሕመምና በአካል ውስጥ ባሉ አንዳንድ ክፍሎች በሚደርሱ ጉዳቶች፣ የቀዶ ጥገና ህክምና የመስጠት ሙያ ያላቸው ዶክተሮች ከፍተኛ ደመወዝ እንደሚከፈላቸው የዌልዝ ሰርክል ድረ ገጽ በ2021 ያወጣው መረጃ አመላክቷል።
እንደ ዌልዝ ሰርክል መረጃ ከሆነ፤ የዓለም ታላቁ ዶክተር በመባል የሚታወቀው እ.ኤ.አ በ1952 ሐምሌ 29 የተወለደው አሜሪካዊ ፓትሪክሱን ሾይንግ (ዶ/ር) በዊትወርስራንድ ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ጥገና ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በዓለም ላይ ካሉት ዶክተሮች መካከል ከፍተኛ ደመወዝ በመከፈል የሚጀመሪያውን ደረጃ ይዟል።
ፓትሪክ እስካሁን 13 ቢሊዮን ዶላር ደመወዝ በመከፈል የመጀመሪያውን ደረጃ ሲይዝ በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ያጠናቀቀው ቶማስ ቀዳማዊ በመባል የሚታወቀው ዶክተር 9.1 ዶላር በመከፈል በዓለም ኹለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ከእነዚህ አስር በዓለም ውስጥ ከፍተኛ ደመወዝ ከሚከፈላቸው ታዋቂ ዶክተሮች መካከልም ፓል ናሲፍ በአስረኛ ደረጃ እንደሚገኝ ነው ድረ ገጹ ያመላከተው።


ቅጽ 3 ቁጥር 155 ጥቅምት 13 2014
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com