የእለት ዜና

በባለፉት ሦስት ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርቶች 333.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተነገረ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በባለፉት ሦስት ወራት ወደ ተለያዩ የዓለም አገራት ከተላከ 88,920.66 ቶን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት 333.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታውቋል፡፡
በሦስት ወራት ውስጥ ታቅዶ የነበረው 74,700.36 ቶን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 245.70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት እንደነበር የገለጸው ባለሥልጣኑ፣ የተገኘው አፈጻጸም ታቅዶ ከነበረው አንጻር ሲታይ በመጠን 14,220 ቶን፣ በገቢ ደግሞ 88 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጭማሪ ማስመዝገቡን ነው የገለጸው፡፡
በዚህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 32,031.71 ቶን (56.31 በመቶ) በገቢ ደግሞ 144.49 ሚሊዮን ዶላር (76.45 በመቶ) ጭማሪ ያሳየ መሆኑን አስረድቷል፡፡
ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የቡና ኤክስፖርት አፈጻጸሙ ደግሞ 70,880.90 ቶን ቡና ተልኮ 239.84 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ ክንውኑ 86,288.14 ቶን ቡና ተልኮ 327.87 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ ታውቋል፡፡
ይህም በመጠን ከ15ሺህ ቶን በላይ እና በገቢ ደግሞ ከ 89 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጭማሪ የተገኘበት ሲሆን፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 32,845.09 ቶን፣ በገቢ ደግሞ 143.08 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማስመዘገቡ ተገልጿል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 156 ጥቅምት 20 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!