የእለት ዜና

10 ከፍተኛ የውልደት መጠን ያላቸው የአፍሪካ አገራት

ምንጭ፡- ስታቲስታ 2021

የስታቲስታ ድረ ገጽ በ2021 ባመላከተው መረጃ መሰረት የወሊድ መጠን ማለት እንድ ሴት የምትወልዳቸው አማካኝ የልጆች ቁጥር ነው። ድረ ገጹ በ2021 ያወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ፤ ከላይ የተዘረዘሩት 10 የአፍሪካ አገራት ከፍተኛ የውልደት መጠን ያላቸው ናቸው።
ከእንዚህም መካከል ኒጀር በወሊድ መጠን የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘች ሲሆን፤ በአገሪቱ ውስጥ በምትገኝ አንዲት ሴት ወደ ሰባት የሚጠጉ ልጆች የመራባት መጠን አላቸው።
በዚህም የኒጀር አጠቃላይ የህዝብ ብዛት በማደጉ በዓለም ላይ ካሉት አስር ከፍተኛ የወሊድ መጠን ያላቸው አገሮች አንዷ መሆኗን ነው መረጃው ያመላከተው። ከኒጀር ቀጥላም አንጎላ 5.9 ፐርሰንት የውልደት መጠን በማስመዝገብ ኹለተኛውን ደረጃ የያዘች ሲሆን፤ ቡሩንዲ 5.1 የውልደት መጠን በማስመዝገብ የ10ኛውን ደረጃ ይዛለች።
በመረጃው ምልከታ መሰረት በአሁኑ ጊዜ በአንድ ሀገር ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር መጨመር ከደካማ ኢኮኖሚ የግንዛቤ እጥረት እና የመከላከያ እርምጃዎች ወይም ደካማ የኑሮ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ምክንያት መሆኑን መረጃው አመላክቷል። የወሊድ መከላከያ አለማግኘትም ለከፍተኛ የወሊድ ምጣኔ አስተዋፅኦ ሳይደርግ እንዳልቀረ ነው ድረ ገጹ የጠቆመው።


ቅጽ 4 ቁጥር 158 ሕዳር 4 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com