የእለት ዜና

ገዳ ኢኮኖሚክ ዞን ተቋቋመ

በቅርቡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መናኸሪያ ይሆናል ተብሎ የታለመለት ገዳ የኢኮኖሚክ ዞን ዕውን ሊሆን መሆኑ ተገለጸ።
ከአዲስ አበባ በ 77 ኪሎሜትር ርቀት በኦሮሚያ ክልላዊ አተዳደር ሥር በምትገኘው ሞጆ ከተማ በ 23ሺሕ 656 ያርፋል ተብሎ የታመነው ዞን ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ እስከ 7 ሚሊዮን ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተነግሯል።
የደረቅ ወደብ መናኸሪያ የሆነችው ሞጆ ከተማ የታቀደላት ዘመናዊ ከተማን ገንብቶ ለመጨረስ እስከ 40 ዓመት ሊፈጅ እንደሚችል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ለሆኑት ዣኦ ዢዩአን በጉብኝታቸው ወቅት ገለፃ ተደርጓል።
ይህ ዘመናዊ ከተማ በተለያዩ ምዕራፎች የሚገነባ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ከ 5 እስከ 10 አመት እንደሚፈጅ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ የገበያ ማዕከሎች እና መዝናኛዎችን እንደሚጨምር ተጠቁሟል።


ቅጽ 4 ቁጥር 158 ሕዳር 4 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!