የእለት ዜና

የስኳር ዕጥረትን ለመቀነስ የኹለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ግዥ ተፈጽሟል

የስኳር አቅርቦት ዕጥረትን ለማሻሻል የኹለት ሚሊዮን ኩንታል የስኳር ግዥ መፈጸሙን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቀ።
በዚህም ከውጭ አገር ግዥ የተፈጸመበት 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ወደ አገር ውስጥ መግባቱ ተነግሯል። ከዚህ ውስጥ 417 ሺሕ ኩንታል የተሠራጨ ሲሆን፣ በቀጣይም 1 ሚሊየን ኩንታል ለማስገባት ግዥ ተፈጽሟል ነው የተባለው።
እንዲሁም በአሁኑ ወቅትም የአገር ውስጥ ምርት 123 ሺሕ ኩንታል ስኳርን ጨምሮ በአጠቃላይ 706 ሺሕ ኩንታል ስኳር ክምችት መኖሩን ተጠቁሟል።
ለክልሎች በወር 300 ሺሕ ኩንታል፣ እንዲሁም ለአዲስ አበባ 120 ሺሕ ኩንታል በድምሩ 420 ሺሕ ኩንታል ስኳር የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ በነበረው የስኳር ዕጥረት ምክንያት 50 በመቶ ብቻ ሲሠራጭ መቆየቱ ተነግሯል። ነገር ግን፣ በአሁኑ ወቅት የአገር ውስጥ ፋብሪካዎች ወደ ምርት በመግባታቸው ሙሉ ኮታው እየተሠራጨ እንደሚገኝ ተገልጿል።


ቅጽ 4 ቁጥር 159 ሕዳር 11 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com