የእለት ዜና

10 ምርጥ የዓለማችን ትላልቅ የአየር ማረፊያዎች

ምንጭ፡- ኤሮታይም 2021

የኤሮታይምስ ድረ ገጽ በ2021 ባመላከተው መረጃ መሰረት የተሳፋሪዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ብዙ አየር ማረፊያዎችን እንዲጨናነቁ አድርጓል። በመሆኑም ሁሉንም አውሮፕላኖች አንድ ቦታ ላይ ለማቆም አስቸጋሪ ሆኖ በመገኘቱ፤ በዓለም ውስጥ የሚገኙ አገሮች አዳዲስ ተርሚናሎችና ማኮብኮቢያዎች ማስፋፋት መጀመራቸውን ኤሮታይምስ ድረ ገጽ ያወጣው መረጃ ጠቁሟል።
በአዲስ መልኩ ከተስፋፉት ውብና ትላልቅ የአየር ማረፊያዎች መካከልም ከላይ የተዘረዘሩት በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችን የሚያስተናግዱና በየ ቀኑ ከመቶ ያላነሱ አውሮፕላኖችን የሚያስተናግዱ መሆናቸው ተመላክቷል።
በዚህም መሰረት ኪንግ ፋህድ የተሰኘው አውሮፕላን ማረፊያ የሳዑዲ፣ የሳዑዲ ገልፍ አየር መንገድ እና ፍሊናስ ማእከል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፤ 776 ካሬ ኪ.ሜ በመሸፈን በስፋቱ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ከዚህም ቀጥሎ በኹለተኛ ደረጃ የሚገኘው የዴንቨር አየር ማረፊያ ሲሆን፤ አንድ ተርሚናልና ስድስት ማኮብኮቢያዎች በመገንባት 135 ካሬ ኪ.ሜ ቦታ ላይ ተንጣሎ ይገኛል።


ቅጽ 4 ቁጥር 159 ሕዳር 11 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com