የእለት ዜና

በ2014 ሩብ ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪው ከ117 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪው ከ117 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ገምግሟል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከዘርፉ ከ125 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ፣ 117 ነጥብ 84 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የሚኒስቴሩ የዕቅድ ዳይሬክተር መንግሥቱ ህሉፍ አብራርተዋል።
በሩብ በጀት ዓመቱ የተገኘው ገቢም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ24 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አያይዘው ተናግረዋል። በቀጣይም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማምረት አቅምን ማጎልበት ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሠራል ነው ያሉት።
የግብዓት አቅርቦትና የውጭ ምንዛሬ ዕጥረትን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ደግሞ መፈታት የሚገባቸው የዘርፉ ማነቆዎች መሆናቸውን ተጠቁሟል።
ሚኒስትር ዴኤታው ሺሰማ ገብረስላሴ በበኩላቸው፣ በአገሪቱ ዘርፉን ለማልማት ያሉ ዕድሎችንና አማራጮች ለመጠቀም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፉ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው ድርሻ የተሻለ እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 160 ሕዳር 18 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!