የእለት ዜና

የጀርመን ኤምባሲ የነጋሪት ጋዜጣ ሥብስቦችን ለቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት አስረከበ

በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ፣ በአዲስ አበባ ለረጅም ጊዜያት በመዝገብ ቤት ውስጥ በጥንቃቄ ይዞ ያቆያቸውን እና ከ1942 ጀምሮ የታተሙ ሙሉ የነጋሪት ጋዜጣ ዕትሞችን ለኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ባለፈው ሳምንት ማስረከቡን ገለጸ።
የቤተ መዛግብቱ ሠነድ አሥተዳደር ዳይሬክተር ሰለሞን ጠና፣ በጀርመን ኤምባሲ በመገኘት የጀርመን አምባሳደር በኢትዮጵያ ከሆኑት ስቴፈን አውር ነጋሪት ጋዜጦቹን መረከባቸው ተገልጿል።
የጀርመን ኤምባሲ የኢትዮጵያን ቅርሶች ጠብቆ ለማቆየት በሚደረገው ሥራ የሁልጊዜ አጋርነቱን መግለጹን ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 164 ታኅሣሥ 16 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!