የእለት ዜና

ለዲያስፖራ አባላት ከታህሳስ 20 ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው ገለጸ

ሰኞ ታህሳስ 18/ 2014 (አዲስ ማለዳ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቀረበውን “በታላቁ ጉዞ ወደ አገር ቤት” ጥሪ ተከትሎ ወደ አገር ቤት የሚመጡ የዲያስፖራ አባላትን በወዳጅነት አደባባይ ከታህሳስ 20 ቀን ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግና ዋና ዋና ዝግጅቶችንም ብሔራዊ ኮሚቴው ይፋ አድርጓል።

እንግዶች በአዲስ አበባ ከተማና በክልሎች በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ ጉብኝቶች፣ ባዛሮች፣ ፌስቲቫሎችና ሌሎችም ሁነቶች መዘጋጀታቸውንም ኮሚቴው አስታውቋል።

ገናን በላሊበላ እንዲሁም ጥምቀትን በጎንደር ለማክበርም ዝግጅት ተደርጓል መባሉንም ኢብኮ ዘግቧል።

ጥር 1 ቀንም በአንድነት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ የሚኖር ይሆናል ተብሏል።

ለዲያስፖራ አባላቱ የተዘጋጁ ዋና ዋና ዝግጅቶች እስከ ጥር 6 የሚቀጥል ሲሆን ሌሎችም ሁነቶች በቀጣይም እንደሚኖሩ ተገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!