የእለት ዜና

በህገ ወጥ የመሬት ወረራ በተሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱ ተገለፀ

ሰኞ ታህሳስ 18/ 2014 (አዲስ ማለዳ) በህገ ወጥ የመሬት ወረራ በተሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ጀማል አላዬ በሰጡት መግለጫ፤ በህገ ወጥ የመሬት ወረራ በተሳተፉ 88 አመራሮችና ሰራተኞች ላይ ፓለቲካዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

ከ26 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው እና በህገ ወጥ የተያዙ 671 ይዞታዎች ካርታቸው እንዲመክን በማድረግ ወደ መሬት ባንክ መመለሳቸውንም ተገልጿል።

ህዝቡ በህገ ወጥ ደላሎች እንዳይታለልና በመንደር ውል የሚደረግ የመሬት ገዥ ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አውቆ የመሬት ግዢ ሲፈፅም በመሬት ውልና ማስረጃ ተቋም በመቅረብ እንዲገዛም ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!