የእለት ዜና

በ104 ሚሊዮን ብር በይርጋለም የተቋቋመው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

‹ዋይ ቢ ኤም› የተሰኘው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ በ104 ሚሊየን ብር በይርጋለም ግብርና ማቀነባበርያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተቋቋመና የአቮካዶ ዘይት በማምረት ወደ ውጭ የሚልክ ነው።
ፋብሪካው ለአካባቢው አርሶ አደሮች ቋሚ ገቢ መፍጠር ያስቻለ ሲሆን፣ ከ40 ሺሕ ገበሬዎች ጋር ትስስር በመፍጠርም አቮካዶን ወደ ዘይት በመቀየር ወደ አውሮፓ እንደሚልክ ተገልጿል።
ፋብሪካው ሥራ ከጀመረ ኹለት ሳምንት ያስቆጠረ ሲሆን፣ ምንም ዓይነት ግብዓት ከውጭ ማስገባት ሳያስፈልግ የውጪ ምንዛሬን በማስገኘት ረገድ ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ ነውም ተብሎለታል።
በይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከሦስት ዓመት በፊት ሥራ የጀመረው ሌላኛውና ኹለተኛ የሆነው ‹ሳንቫዶ› የተሠኘው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ፣ ከ88 ሺሕ አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠር፣ ምርት በመሰብሰብና ለግብዓትነት በመጠቀም፣ ያመረተውን የዘይት ምርት ወደ ኔዘርላንድ እየላከ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 165 ታኅሣሥ 23 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!