የእለት ዜና

ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ላይ ባሰማኋቸው ምስክሮች ብይን ይሰጥልኝ አለ

ሰኞ ታህሳስ 25/2014 (አዲስ ማለዳ) ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ላይ ባሰማኋቸው ምስክሮች ብይን ይሰጥልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ።

ዐቃቤ ህግ አሉኝ ብሎ በክሱ ላይ ከጠቀሳቸው ምስክሮች ውስጥ 6 ምስክሮን ያሰማ ሲሆን 7ኛ ምስክር በተደጋጋሚ በተሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ አለመቅረቡን ተከትሎ በፖሊስ ታስሮ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ቢሰጥም ትዕዛዙ ሳይፈጸም፤ ምስክሩም ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡

ችሎቱም በተደጋጋሚ ቀጠሮ ላልቀረበው ምስክር በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም ሲል ብይን ሰጥቷል።

በዚሁም መሰረት ዐቃቤ ሕግ እስካሁን ባሰማኋው ምስክሮች እና ባቀርብኳቸው ማስረጃዎች መሰረት ብይን ይሰጥ ብሎ መጠየቁን ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥር 25 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!