የእለት ዜና

“በማለዳው የአረንጓዴ አሻራቸውን ማኖሪያ ፓርክ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ሥም ሰይመናል”:-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ማክሰኞ ታህሳስ 26/2014 (አዲስ ማለዳ) “ዛሬ በማለዳው የአረንጓዴ አሻራቸውን ማኖሪያ ፓርክ በዳያስፖራው ማህበረሰብ ሥም ሰይመናል። በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አነሳሽነት የተጀመረው ኢትዮጵያችንን አረንጓዴ የማልበስ ተግባር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት ነው።” ሲሉ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

በመዲናዋ የዳያስፖራ ፓርክ በአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ተከፍቷል።

ዳያስፖራዎችም በፓርኩ ዉስጥ የተለያዩ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸዉን ያኖሩ ሲሆን፤ 4 ሺህ በላይ ችግኞች በዳያስፖራዎቹ መተከላቸውም ታውቋል።

ይህንንም በማስመልከት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስርገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ይህ ፓርክ ትርጉሙ ከአረንጓዴ ልማት በላይ ነው። በውጭው ዓለም ኢትዮጵያ ጫና ሲደርስባት ዳያስፖራው አቅሙን ሳይሰስት ትግል ሲያደርግ ቆይተዋል። ትውልድ እንዲማርና ወቅቱን እንዲያስብ እንዲሁም አካባቢን ለማልማት ለዳያስፖራው ማስታወሻ የሚሆንም ነው።” ብለዋል።

አክለውም የዳያስፖራው የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎንም ያበረታታል ያሉ ሲሆን፤ “በቀጣይም መሰል ተሳትፎዎችን በማጉላት አገርን በሁሉም መስክ ለመደገፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚወጡ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉም ገልፀዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!