የእለት ዜና

ፌልትማን ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ሐሙስ ኢትዮጵያ ይገባሉ

ዕሮብ ታህሳስ 27/2014 (አዲስ ማለዳ) የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ሐሙስ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተገለፀ።

ፌልትማን ኢትዮጵያ የሚመጡት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሰላም ድርድር ጉዳይ ለመነጋገር እንደሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ አስታውቀዋል።

አምባሳደር ፌልትማን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ቢገለፅም እነማንን እንደሚያገኙ ምንም የተጠቀሰ ነገር የለም።

አምባሳደር ፌልትማን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ወደ ትግራይ ክልል ይሄዱ እንደሆነ ፕራይስ ተጠይቀው፤ ለአሁን መናገር የሚችሉት አምባሳደሩ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር እንደሆነ አመልክተዋል።

ቃል አቀባዩ ፥ በውይይቱ ዝርዝር ላይ መናገር የሚችሉት በማጠቃለያው እንደሆነ እና ዝርዝሩንም በፅሁፍ እንደሚያወጡ ገልፀዋል ሲል የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

ፕራይስ ፥ አምባሳደር ፌልትማን ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር እንዲነጋገሩ አሁን ያለው ሁኔታ አመቺ መሆኑን ጠቁመው ሁለቱም ወገኖች ውጊያ እንዲያቆሙና ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲቀርቡ ዕድል እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

አምባሳደር ፌልትማን ኢትዮጵያ ሲገቡ የውይይቱ ይዘት ይኸው እንደሚሆን ገልፀዋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማ ከዚህ ቀደም የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ዘንድ ጥረት ለማድረግ በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወቃል።
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!