የእለት ዜና

“ሁልጊዜ የማስባትን አገሬን በማየቴ ደስ ብሎኛል” ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

ዕሮብ ታህሳስ 27/2014 (አዲስ ማለዳ) የመንግሥትን የ1 ሚሊዮን ዲያስፖራዎች ጥሪ ተቀብላ ኢትዮጵያ የገባችው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ “ሁልጊዜ የማስባትን አገሬን በማየቴ ደስ ብሎኛል” ብላለች፡፡

በ#NoMore ዘመቻ የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም ያሳወቀችው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብታለች።

“ስለተሰጠኝ ፍቅርና ስላደረጋችሁልኝ አቀባበል አመሠግናለሁ” ያለችው ጋዜጠኛ ሄርሜላ “ለዚች አገር ብሩህ ተስፋ ነው የሚታየኝ፤ ሁሉም ሰው ያደረገው የ#nomore (በቃ) እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው” ማለቷን ዋልታ ዘግቧል፡፡

ጋዜጠኛዋ ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ አቀባበል አድርገውላታል።
_______
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!