የእለት ዜና

የዲጂታል መታወቂያ ህትመትና ሥርጭት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

ዕሮብ ታህሳስ 27/2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እንደገለጸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በማዕከል ደረጃ በማህተም ለሁሉም ክፍል ከተማ ሲያሰራጭ የነበረውን አሰራር ቀይሮ ህትመቱ በከተማ ባሉ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ደረጃ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኤጀንሲው የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቱ አንድ ነዋሪ አንድ የነዋሪነት መታወቂያ ብቻ እንዲኖረዉ ማድረግ እንደሚያስችል አስታውቋል::

ይህ ሥርዓት ለነዋሪዎች የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ላይ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑንም ኤጀንሲው ገልጿል::

ኤጀንሲው አገልግሎቱን ወደ ሥራ ከማስገባቱ አስቀድሞ ለሁሉም ክፍለ ከተማ የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያዎች ሥልጠናን መስጠቱንም አስታውቋል::

ህትመትና ሥርጭት ወደ ክ/ከተማ መውረዱ ተገልጋዩ ህብረተሰብ የመታወቂያ ህትመት ለመውሰድ የሚፈጅበትን ጊዜ እና ገንዘብ እንደሚያስቀርና በማሽኖች ላይም የሚደርሰውን የስራ ጫና በመቀነስ የማሽን ብልሽትን እንደሚቀርፍም ተጠቁሟል::
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!