የእለት ዜና

ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ እንደሚገኝ ተገለፀ

ዕሮብ ታህሳስ 27/2014 (አዲስ ማለዳ) አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው የጉሙሩክ ኮሚሽን አሳውቋል።

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከህመማቸው ተፈውሰው የሚወዱትን ሙያ እንዲቀጥሉ እና አገራቸውን በኪነጥበብ መስክ እንዲያገለግሉ መልካም ምኞታቸውን እንደገለፁላቸው ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የመድረክ ፈርጥ በመሆን እና በአጫዋወት ስልቱ ለኦሮምኛ ሙዚቃ ብሎም ለአገራችን የሙዚቃ እድገት የራሱን ጉልህ አሻራ ማስቀመጡ ይታወቃል።

ለሙዚቃ እድገት ባበረከተው አስተዋጽኦም የክብር ዶክትሬትን ጨምሮ ሌሎች አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘ ታላቅ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነው፡፡
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!