የእለት ዜና

“ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች በይቅርታ እየተፈቱ ነው”፡-የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

ዕሮብ ታህሳስ 27/2014 (አዲስ ማለዳ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ከሽብር ቡድኖች ጋር መስራታቸው አገርን እንደ መካድ የሚቆጠር መሆኑን አምነውና በድርጊታቸው ተጸጸተው ይቅርታ በመጠየቃቸው ከእስር እየተፈቱ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሰታወቀ፡፡

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ ከተለያዩ የሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የተጠረጠሩ ሰዎችን የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ይታወሳል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሠ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በጸጥታ አካላት ተጠርጥረው ከታሰሩት ውስጥ የጥፋት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆነና መንግስት ከጥፋታቸው ተገቢውን ትምህርት ወስደዋል መንግስት ጉዳዮን በሆደ ሰፊነት አይቶ የለያቸው በርካታ ሰዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ አድርጓል ብለዋል፡፡

የቀሩትም እንደ ሁኔታው የጥፋት ደረጃቸው እየታየ ቀጠይ የሚለቀቁ እንደሚሆን ገልጸው፤ቁልፍ የችግሩ ተዋንያን የሆኑት ደግሞ ጉዳያቸው ተጣርቶ ለፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የመንግስት ዓላማ አስተማማኝ፣ ዘላቂ ሠላም አስፍኖ የህግ የበላይነት እንዲረጋጋጥ ማስቻል ነው ያሉት ዶክተር ለገሠ፤ ይህንን የሚገዳዳር ማናቸውን እንቅስቃሴዎች ከህግ ተጠያቂነት አያመልጥም ሲሉም ገልፀዋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!