የእለት ዜና

“በድል ማግስት ለሚከበረው የገና በዓል እንኳን አደረሳችሁ”፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት

ሐሙስ ታህሳስ 28/2014 (አዲስ ማለዳ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በድል ማግስት ለሚከበረው የገና በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ገለጸ፡፡

በዓሉን ተከትሎ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ የኢትዮጵያዊያን ዕሴቶች የሆኑትን ፍቅርንና አንድነታችን በማጠናከር መከበር እንደሚገባው ምክር ቤቱ አመልክቷል፤ ኢትዮጵያዊ ጨዋ ባህላችንን የሚሸረሽር መለያየትና ጥላቻን በመቅበር፣ለጋራ ዓላማ በመትጋት፣ የተቸገሩትን በመታደግ በዓሉ ሊከበር እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞና ትንሳዔ በሚያፋጥኑ ላይ በሚደረገው ርብርብ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቤት የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጎላ ድርሻ ያለው በመሆኑ፣ ምክር ቤቱ የተጣሉበትን አገራዊ ኃላፊነቶች እንዲወጣ ሁሉም በተሠማራበት የበኩልን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ የተቃጣውን አገር የማፍረስ ሴራ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት መክተን ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆነ ቀጥላለችም ብሏል ምክር ቤቱ በመልዕክቱ።

በዓሉ ለኢትዮጵያዊያን ድርብ ደስታ የፈጠረ ሲሆን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዓሉን ከእኛ ጋር ለማክበር በመምጣታቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች አንገታቸውን ደፍተዋል ብሏል።

በመጨረሻም በዓሉ ለኢትዮጵያዊያን የብልጽግና፣ የደስታ፣ የሠላምና የአንድነት እንዲሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መልካም ምኞቱን ገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!