የእለት ዜና

“የጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የስልክ ውይይት የፖለቲካ ሁነቱ መቀየሩን ማሳያ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሐሙስ ጥር 5 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሳምንቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የስልክ ውይይት የፖለቲካ ሁነቱ እንደተቀየረ ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ እንዳሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ ውይይት አድርገዋል። ይህ ውይይት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን የስልክ ውይይቱ የፖለቲካ ሁኔታው እየተቀየረ ስለመሆኑ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።

በሳምንቱ የዲያስፖራ አንቅስቃሴ ላይ ትልልቅ መድረኮች እንደተካሄዱም አብራርተዋል።

የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴን ለማሳደግ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ብቻ ሳይሆኑ አፍሪካውያንም ተሳትፈውበታል ብለዋል።

ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ዲያስፖራው ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር መምከሩንም አምባሳደር ዲና አስረድተዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም ሚናቸውን በሚያሳድጉበት ዙሪያም ምክክር መደረጉን የተናገሩት አምባሳደር ዲና ዲያስፖራው በላልይበላ የልደት በዓልን እንዳከበረ ሁሉ አሁንም በጎንደር ጥምቀትን ለመታደም በርካታ ዝግጅቶች እንደተደረጉ ነው የገለጹት።

ይህም ፀረ ኢትዮጵያ ኀይሎች ይነዙት የነበረውን የሀሰት ወሬ ትርጉም አልባ እንዲሆን አድርጎታል ሲሉም ገልፀዋል።
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!