የእለት ዜና

ቅዱስ ሲኖዶሱ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ላይ ሊያደርገው የነበረው ስብሰባ ተራዘመ

አርብ ጥር 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባጋጠመቸው የጤና እክል ምክንያት ስብሰባው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው፣ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።
_____________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!