የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከታክስ በፊት 8 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር አተረፈ

0
902

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2011 በጀት ዓመት ወደ ተለያዩ የአለም አገራት ባሉት መዳረሻዎቹ በመብረር ከሰጠው አገልግሎት 8 ነጥብ 9 በሊዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ ማስመዝገቡ ታወቀ። አየር መንገዱ ዕቃዎችን እና መንገደኞችን ከማጓጓዝ ባለፈም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን በመስጠቱ 114 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ ለትርፉ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረገለት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።

የአየር መንገዱ የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በኢጀንሲው በተገመገመበት ወቅት እንደተገለፀው፥ ከአየር መንገዱ አጠቃላይገቢ ውስጥ 3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር በውጭ ምንዛሪ የተገኘ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በየነ ገብረመስቀል በግምገማው ወቅት እንደተናገሩት አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ ያጋጠመውን የአውሮፕላን መከስከስ ተቋቁሞ ይህን ያህል ትርፍ ማስመዝገቡ የሚያስመዘግበው እንደሆነ ገለፀዋል። አየር መንገዱ በ2012 በጀት ዓመትም የአገልግሎት አሰጣጡን እና አድማሱን በማሳደግ 155 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘትና 19 ቢሊዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ ለማስመዝገብ ማቀዱም ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here