የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በአጋጠመው ችግር ሴኔጋል ዳካር አርፏል

0
855

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን ከሴኔጋል ዳካር ብሌይስ ዳጊን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ ሞተሩ በእሳት በመያያዙ በአስቸኳይ ለማረፍ ተገዷል። አውሮፕላኑ ከሴኔጋል ዳካር በማሊ ባማኮ ወደ አዲስ አበባ ለማቅናት ብሌይስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያን እንደለቀቀ ነበር የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ የቀኝ ሞተሩ በእሳት መያያዙን ለአየር ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት በማድረግ በአስቸኳይ ያሳረፈው።

ዘጠና መንገደኞችን እና የአውሮፕላን ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን በድንገት መረፍ ተከትሎ በርካታ የአደጋ ጊዜ እና የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስፍራው በመገኘት አስፈላጊውን ስራ የሰሩ ሲሆን በአውሮፕላኑ ውስጥ ባሉ ሰዎች ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም ለማወቅ ተችሏል።

የበረራ ቁጥር ኢቲ 908 አውሮፕላን የበረራ ሁኔታው መስተጓጎሉን በማስመልከት ኢትዮጵያ አየር መንገድ በትዊተር ገፁ ይቅርታ በመጠየቅ የተፈጠረ የቴክኒክ ችግር መኖሩንም ይፋ አድርጓል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here