ብርሃንና ሰላም የሕትመት ስራዎችን ሊያቆም እንደሚችል አስታወቀ

0
389

ዕድሜ ጠገቡ ማተሚያ ቤት ብርሃንና ሰላም ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር በተያያዘ ከኹለት እና ሦስት ወራት በኋላ አገልግሎት መስጠት እንደሚያቆም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘግቧል። ማተሚያ ድርጅቱ ለሕትመት የሚሆኑ ግብዓቶች እንደ ቀለም፣ ወረቀት ፕሌት እና የተለያዩ አይነት ኬሚካሎች ከውጭ ስለሚያስገባ እና የተፈጠረው የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ደግሞ ትልቅ ተግዳሮት ስለሆነበት ችግሩ ካልተቀረፈ ከጥቂት ወራት በኋላ ሕትመት ለማቆም እንደሚገደድ አስታውቋል።

ብርሃንና ሰላም ከተጠቀሱት ግብዓቶች በተጨማሪም የመለዋወጫ ዕጥረት በሰፊው ያጋጠመው ሲሆን ይህንም ለመቅረፍ በተደጋጋሚ ከአንድ ዓመት በላይ ለብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ እንዲፈቀድለት ቢያሳውቅም ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱን ገልጿል። ከተፈጠረው ችግር አንፃር ጋዜጦችን እና ሌሎች ሕትመቶችን በሕትመት ወረቀቶች እያተመ እንዳልሆነና አሁን ያለው የወረቀት ክምችትም ከኹለት ወራት በላይ እንደማያሰሩት አስታውቆ፤ ብሔራዊ ባንክ ለችግሩ መፍትሔ ካላበጀለት የሕዝብ ልሳን የሆኑ ጋዜጦችና አገር አቀፍ ፈተናዎች መታተም እንደማይችሉ የድርጅቱ የኮርፖሬት በዝነስ ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ነጋሽ ለአዲስ ዘመን ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here