መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናኢሰመኮ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች...

ኢሰመኮ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመሩን በበጎ እንደሚቀበለው ገለጸ

አርብ ነሐሴ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመር እና የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በበጎ እንደሚቀበለው ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በአፋር ክልል፣ ሰመራ ከተማ የሚገኙትን አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች በተመለከተ ያካሄደውን ክትትል እና ያወጣውን ሪፖርት በማስታወስ፣ ይህንኑ ተከትሎ በካምፖቹ የነበሩ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው የመመለሱ ተግባር መጀመር እና የባንክ አገልግሎት ማግኘትን ጨምሮ ሌሎች እየተደረጉ ያሉ ሰብአዊ ድጋፎችን በበጎ ተመልክቷል ብለዋል።

እንዲሁም፤ ኮሚሽኑ በአማራ ክልል፣ ወሎ የሚገኙትን የጃራ እና የጃሬ ካምፖች በተመለከተ ምርመራ እያካሄደ ሲሆን፤ ከአስተዳደራዊ እና የፀጥታ አካላት እያሰባሰበ ያለውን መረጃ የሚያካትት ሪፖርት በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑንም ዶ/ር ዳንኤል ጨምረው ገልጸዋል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች