የኢትዮጵያ እና የኬንያ አየር መንገዶች ወደ ደቡብ ሱዳን ሚያደረጉትን በረራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አስታወቁ

0
485

የኢትዮጵያ እና የኬንያ አየር መንገዶች በአየር መንገድ ሰራተኞቻቸው ላይ እንግልት እየደረሰ በመሆኑ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርጉትን በረራ ሊያቋርጡ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። የደቡብ ሱዳን የትራንስፖርት ሚኒስትር ጆን ሎክ ጆክ እንዳስታወቁት፤ ከኹለቱ አየር መንገዶች ቅሬታዎች እንደደረሳቸው እና እንደምክንያት ደግሞ የቀረበው በጁባ አየር ማረፊያ እየደረሰ ያለው በአየር መንገዶች ሰራተኞች ላይ እንግልት እንደሆነ አስታውቀዋል።

የሱዳኑ የዜና አውታር ኒያሚልፔዲያ መንግሥት ቃል አቀባዩን ሚካኤል ማኩየን ጠቅሶ እንደዘገበው ጉዳዩ ለመንግሥት ካቢኔ መድረሱንም አስታውቋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ባሳለፍነው ዓርብ ለደቡብ ሱዳን የካቢኔ ስብሰባ ላይ ያስረዱት የትራንስፖርት ሚንስትሩ አልፎ አልፎ በሚከሰቱ የመንገደኞች ሻንጣ መጥፋት ጋር በተያያዘ መንገደኞች በአየር መንገድ ሰራተኞች ላይ ድብደባ እንደሚፈጽሙ አስታውቀዋል። ሚንስትሩ አያይዘው እንደገለፁት በአየር ጉዞ ላይ ሻንጣ መጥፋት የተለመደ እንደሆነና በሌላው ዓለምም የሚያጋጥም መሆኑን ጠቁመው ደቡብ ሱዳንን ልዩ የሚያደርግበት ምክንያት እንደሌለ ገልፀዋል። በሰራተኞች ላይ እንግልት ሲያደርስ የተገኘ ተጠያቂ እንደሚሆን አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here