በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች እንደሚተከሉ ተገለፀ

0
1036

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ 200 የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ ለመትከል በዝግጅት ላይ መሆኑን  አስታወቀ። ባለሥልጣኑ ለመትከል ካሰባቸው የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ውስጥ   በተያዘው በጀት ዓመት ኹሉንም የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች በተለያዩ የከተማዋ አከባቢዎች ለመትከል ዝግጅት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎቹ 8ሚሊዮን 740 ሺሕ ብር ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን ከከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ቦታዎች እንደሚተከሉ የባለሥልጣኑ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ ተናግረዋል። አዲስ አበባ ከተማ እየሰፋች ሲሆን በዚህም ምክንያት አዲስ እየተስፋፉ በመጡ አከባቢዎች መሳሪያ ያልተተከሉባቸውን አከባቢዎች በመለየት መሳሪያዎቹ ይተከላሉ ብለዋል ሲል ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here